በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በዲሞክራቶች የሚመራው ምርመራን "ሊንቺንግ ነው" አሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በርሳቸው ላይ የሚካሄደው በዲሞክራቶች የሚመራው ምርመራን ሊንቺንግ ነው ብለውታል። “ሊንቺንግ” የሚለው ቃል በነጮች የበላይነት የሚያምኑ ነጮች አፍሪካውያን፣ አሜሪካውያንን ለመጨቆን ሲሉ ይጠቀሙበት የነበረ ዘግናኝ የደቦ ዕርምጃ ዘዴ ነው።

በዲሞክራት የምክር ቤት አባላት የሚመራው ምርመራ ፕረዚዳንት ትረምፕ ለምክር ቤታዊ ክስ የሚያበቃ በደል ፈጽመው ከሆነ ለማጣራት ሲሆን ከተከሰሱ ከሥልጣን እስከመወገድ ሊያደርሳቸው ይችላል።

“መላ ሪፖብሊካውያን ሊንቺንግን እያዩ መሆናቸውን ማስታወስ አለባቸው” ሲሉ ትረምፕ ዛሬ በትዊተር ፅፈዋል። “ሆኖም እናሸንፋለን” ሲሉም አስገንዝበዋል።

አከራካሪው የትረምፕ አባባል ወድያውኑ ከዲሞክራቶች የሰላ ሂስ አስከትሏኣል። አንድ ሪፖብሊካዊ ግን ደግፈውታል።

ህገ መንግሥታዊውን ሂደት እኔን በሚመስሉ ሰዎች ላይ ይፈፀም ከነበረው ጭካኔ የተሞላበት የሰቆቃ ተግባር ጋር እያወዳደሩት ነው?” ሲሉ ጥቁር የምክር ቤት አባልት ቡድን ሊቀ መንበር ኬረን ባስ በትዊተር ምላሽ ሰጥተዋል።

የትረምፕ ደጋፊ የሆኑት የሰሜን ካሮላይና ተወካይ ሊንድሲ ግራም ግን ፕረዚዳንቱ ቃሉን መጠቀማቸው ትክክል ነው። ይህ የፖለቲካ ሊንቺንግ ነው ብለዋታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG