በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መባላቸውን አወገዙ


 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
  • ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ በመጠበቅ ላይ ነው

በኒው ዮርክ ከሕዝብ በተውጣጣ ችሎት በ34 የክስ ዓይነቶች ትላንት ጥፋተኛ እንደሆኑ የተወሰነባቸው የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ውሳኔውን “አሳፋሪ” ሲሉ አውግዘዋል።

ትረምፕ ከውሳኔው በኋላ ከፍርድ ቤት ሲወጡ እንደተናገሩት፣ የእርሳቸውን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑት በምርጫ ቀን ድምፅ ሰጪዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

“የተጭበረበረ፣ ክብር የሌለው የፍርድ ሂደት ነው። እውነተኛው ፍርድ በኅዳር 5 ቀን ይሰጣል” ብለዋል ትረምፕ መጪውን የምርጫ ቀን ለማመልከት፡፡

የቀድሞው ፕሬዝደንት ዛሬ ጠዋት ‘ትረምፕ ታወር’ በሚል በሚታወቀው የኒው ዮርክ ሕንፃቸው ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ በመጠበቅ ላይ ነው።

ትረምፕ በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ የመጀመሪያው የቀድሞ ፕሬዝደንት ሆነዋል።

ትረምፕ የተከሰሱት ከ2016 ምርጫ ቀደም ብሎ፣ ለወሲብ ፊልም ተዋናይ ግንኙነታቸውን ይፋ እንዳታወጣ አፍ ማዘጊያ ገንዘብ ከፍለዋል፣ ወጪውንም ለመደበቅ በንግድ ዶሴዎቻቸው ላይ በተጭበረበረ መንገድ አስፍረዋል በሚል ነበር።

ቅጣቱ ከአንድ ወር በኋላ፣ በእ.አ.አ በመጪው ሐምሌ 11 2024 እንደሚሰጥ ታውቋል። ጥፋቱ እስከ አራት ዓመት በእስር የሚያስቀጣ ሲሆን፣ ዳኛው ትረምፕን በእስር ይቅጡ ወይም በአመክሮ ይለፏቸው በዕለቱ የሚታወቅ ይሆናል። በተመሳሳይ ወንጀል ጥፋተኛ ለተባሉ ሰዎች የእስር ቅጣት ያልተለመደ መሆኑን የሕግ ባለሙያዎች በመናገር ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG