በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
ትረምፕ ‘ጎልድ ካርድ’ የተሰኘ የመኖሪያ ፈቃድ ለውጪ ባለሀብቶች በ5 ሚሊዮን ብር እንደሚሸጡ አስታወቁ

ትረምፕ ‘ጎልድ ካርድ’ የተሰኘ የመኖሪያ ፈቃድ ለውጪ ባለሀብቶች በ5 ሚሊዮን ብር እንደሚሸጡ አስታወቁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ

ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ አሜሪካ መጥተው የሥራ ዕድልን መፍጠር ለሚሹ የውጪ ባለሃብቶች ለመኖሪያ ፈቃድ የሚያገለግላቸውን እና ‘ጎልድ ካርድ’ ብለው የሰየሙትን በ5 ሚሊዮን ዶላር መሸጥ እንደሚሹ አስታውቀዋል።

በሁለት ሳምንታት ውስጥ እንዲጀምር በሚሹት የስደተኞች ፕሮግራም የሚሸጠው ‘ጎልድ ካርድ’ በቀጥታ የግሪን ካርድ ባለቤት እንደሚያደርግና ዜግነት ለማግኘት የሚደረግው ሂደት አካል እንደሚሆን አስታውቀዋል።

‘ጎልድ ካርድ’ ያላቸው ባለሀብቶች በአሜሪካ ለመሥራት፣ የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ኩባንያዎችን ለመመስረትና እንዲችሉ እንዲሁም ታክስም እንደሚከፍሉ አስታውቀዋል።

ኩባንያዎች የተማረ የሰው ኅይል ወደ አሜሪካ በ’ጎልድ ካርድ’ ሲያስመጡ ወጪውን ይሸፍናሉ ብለው እንደሚጠብቁ ትረምፕ አስታውቀዋል። ሃገራቸውም አንድ ሚሊዮን ጎልድ ካርዶችን ልትሸጥ እንደምትልችልም ትረምፕ አስታውቀዋል።

አዲሱ የጎልድ ካርድ ፕሮግራም ከዚህ በፊት የነበረውን ‘EB-5 የስደተኛ ኢንቨስተሮች ፕሮግራም’ የሚተካ መሆኑም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG