በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍትህ መ/ቤቱ አርባ የፍ/ቤት መጥሪያዎችን ላከ


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና አጋሮችቸው የእአአ 2020 ምርጫን ውጤት ዋጋ ቢስ ለማድረግ ያደረጉትን ጥረት በተመለከተ ማስረጃ ለመሰብሰብ 40 የሚሆኑ የፍ/ቤት መጥሪያዎችን የአሜሪካው የፍትህ መስሪያ ቤት ልኳል ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

የትረምፕ የረጅም ግዜ አማካሪ የነበሩት ቦሪስ ኢፕስቲን እና የምርጫ መሃንዲሳቸው ማይክ ሮማን ባለፈው ሳምንት የእጅ ስልካቸው ለማስረጃ በሚል መነጠቁን ኒው ዮርክ ታይምስ ጨምሮ ዘግቧል።

የትረምፕ የማኅበራዊ ሚዲያ መሪ ዳን ስካቪኖ እና ሌሎች በታችኛው እርከን ላይ ያሉ አማካሪዎች በፍ/ቤት መጥሪያው መካተታቸውን ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል።

የፍርድ ቤት መጥሪያዎቹ የተላኩት በትረምፕና አጋሮቻቸው የእአአ 2020 ምርጫን ውጤትን ለመገልበጥ አማራጭና ሃሰተኛ የምርጫ ወኪሎችን ዝርዝር ለማቅረብ ያደረጉት የከሸፈ ሙከራን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃን ለመፈለግም ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም በጥር 6/2021 በአሜሪካ ም/ቤት ላይ በትረምፕ ደጋፊዎች የተፈጸመውን ጥቃት በተመለከተም መረጃ ለማሰባሰብ ነው ተብሏል።

አንዳንዶቹ መጥሪያዎች፣ በፍትህ መ/ቤቱ በአዲስ መልክ የተያዘውና፣ በትረምፕ የሚመራው “አሜሪካንን እናድን” የሚለው ፖለቲካዊ የገንዘብ አሰባሳቢ ቡድንን በተመለክተ ለሚደረገው ምርመራ ማስረጃ ለማሰባሰብ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG