በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒው ኦርለንስና ቴክሳስ አውሎ ንፋስ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ


በኒው ኦርለንስና አካባቢው ላይ ትናንት ማክሰኞ በደረሰው ትልቅ የአውሎ ንፋስ ወጀብ የንብረት ውድመት ሲያደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ተነግሯል።
በኒው ኦርለንስና አካባቢው ላይ ትናንት ማክሰኞ በደረሰው ትልቅ የአውሎ ንፋስ ወጀብ የንብረት ውድመት ሲያደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ተነግሯል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኒው ኦርለንስና አካባቢው ላይ ትናንት ማክሰኞ በደረሰው ትልቅ የአውሎ ንፋስ ወጀብ የንብረት ውድመት ሲያደርስ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ተነግሯል፡፡

ውድመቱ የደረሰው ከ17 ዓመት በፊት በደረሰው የካትሪና ወይም ሄሪካን ካትሪና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት አካባቢ ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ባለሥልጣናቱ በጉዳቱ አንድ ሰው መሞቱን ሲገልጹ በርካቶች መቁሰላቸውን አስታውቀዋል፡፡ በሺህዎቹ የሚቆጠሩ ቤቶችና የንግድ ተቋማት የፈራረሱ ሲሆን በኒው ኦርለንስ አካባቢ የኤሌክትሪ ኃይል መቋረጡ ተነገሯል፡፡

በሌላም በኩል ባለፈው ሰኞ በቴክሳስ ደቡባዊ አካባቢ በደረሰ ተመሳሳይ መጠነ ሰፊ ጉዳት አንድ ሰው መሞቱና በርካቶች መቁሰላቸው ተገልጿል፡፡

የቴክሳስ ገዥ ግሬግ አቦት በአውሎ ንፋሱ በተመቱ 16 ቀበሌዎች የአደጋ ጊዜ አዋጅ ማውጣታቸው ተነግሯል፡፡

XS
SM
MD
LG