በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፓምፔዮ በሱዳን


የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ከሱዳን ከፍተኛ የመንግሥት መሪዎች ጋር
የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ከሱዳን ከፍተኛ የመንግሥት መሪዎች ጋር

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ ዛሬ ሱዳን ገብተዋል። የትረምፕ አስተዳደር የአረብ ሀገሮች ለእስራኤል እውቅና እንዲሰጡ፣ እየገፍ ባለበት ወቅት ነው፣ ፓምፔዮ ሱዳንን የጎበኙት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስሩ፣ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክና ከሉአላዊው መማክርት ዋና ሊቀመንበር አብደል ፋታሕ ኤል-ቡርሃን ግር ተግርናኝተው ይነጋገራሉ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚለው፣ ከሱዳንና እስራኤል ግንኙነት ሌላ፣ አሜሪካ ለሱዳን የሽግግር መንግሥት እርዳታ መስጠቱን የምትቀጥል ስለመሆኗም ይነጋገራሉ።

ፓምፔዮ ትናንት ሰኞ ጉብኝታቸውን የጀመሩት በእስራኤል ሲሆን፣ አሜሪካ ከተባበረው የአረብ ኤሚሬቶች ጋር ልታደርግ በምትችለው፣ ማንኛውም ዓይነት የመሳርያ ሥምምነት፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የእስራኤል ወታደራዊ የበላይነት መጠበቁን፣ ታረጋግጣለች ማለታቸው ታውቋል።

XS
SM
MD
LG