በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢራን መንግሥት ላይ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል ታዘዘ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፕዬ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፕዬ

ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ “ደም ማፍሰስ፣ ብጥብጥ እና ቀውስ መቀስቀሱን አባብሶ የቀጠለው ነብሰ ገዳይና አምባገነን” ባሉት የኢራን መንግሥት ላይ ዛሬ ሰኞ ከዕኩለ ለሊት አንስቶ ተፋጻሚ የሚሆን የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ።

ዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ “ደም ማፍሰስ፣ ብጥብጥ እና ቀውስ መቀስቀሱን አባብሶ የቀጠለው ነብሰ ገዳይና አምባገነን” ባሉት የኢራን መንግሥት ላይ ዛሬ ሰኞ ከዕኩለ ለሊት አንስቶ ተፋጻሚ የሚሆን የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ።

ትረምፕ ዛሬ ዳግም መልሰው ያጸደቁት ማዕቀብ፤ ቀደም ሲል በኒውክለር ቅመማ ፕሮግራሟ ሳቢያ በቴሕራን ላይ ተጥሎ የነበረው ማዕቀብ እንዲነሳላት ካደረገውና እአአ በ2015 ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ከስድስቱ ኃያላን አገሮች ጋር ከተደረሰው ስምምነት በተናጠል አገራቸውን ካወጡ ሦሥት ወራት በኋላ የመጣ ነው።

በሌላ ዜና የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፕዬ ባለፈው ቅዳሜ ለጋዜጠኞች በሰጡት መገለጫ፤ ኢራን፣ እንደ እርሳቸውም ቃል “እንደ ጤነኛ አገር” መንቀሳቀስ መጀመር አለባት” ሲሉ አሳስበዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የወሰደችው ይህ እርምጃ በኢራን የኦቶሞቲቭ ፋብሪካዎች፣ የወርቅ፣ የከሰል ማዕድን እና የብረታ-ብረት ማምረቻ እንዱስትሪዎችን ጨምሮ፤ መጠነ ሠፊ ማዕቀብ የሚጥል መሆኑንም ፖምፕዬ አመልክተዋል።

ፖምፕዬ አክለውም “ይሄ ኢራናውያን በገዛ መንግስታቸው ላይ ያላቸውን ቅዋሜ ብቻ የተመለከተ ነው። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ያላቸውን አቋም ግልጽ አድርገዋል። የኢራን ሕዝብ መሪዎቹ እነማን እንዲሆኑ እንደሚፈልግ ድምጹን የማሰማት እንሻለን፤” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG