በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የካናዳና ሜክስኮ ድንበሮችን ልትከፍት ነው


ዩናይትድ ስቴትስ ሙሉ ለሙሉ ለተከተቡ መንገደኞች የካናዳና ሜክስኮ የየብስ ድንበሮችን ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ክፍት እንደምታደርግ ዛሬ ረቡዕ አስታውቃለች፡፡

የሁለቱ አገሮች ወሰኖች የኮቪድ-119፣ ወረርሽኝ ከተሰከተበት እኤአ ከመጋቢት 2020 ጀምሮ፣ ከተወሰኑ እንደ ንግድ ካላኡ መሠረታዊ ነገሮች ውጭ፣ ለሁሉም ተሽከርካሪዎች ለባቡርና ለውሃ ላይ መጓጓዣዎች ዝግ ሆነው ቆይተዋል፡፡

ውሳኔው የመጣው ፕሬዚዳንት ባይደን ከመጪው ወር ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የተከተቡ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መብረር እንደሚችሉ ካስታወቁ አንድ ሳምንት በኋላ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG