በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሃያ ዓመታት የኖሩ የኤል ሳልቫዶር ዜጎች ጉዳይ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሃያ ዓመታት ገደማ ለኖሩና ወደ 262,500 ለሚሆኑ የኤል ሳልቫዶር ዜጎች የተሰጠውን ጊዜያዊ ጥበቃና ከለላ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሊሰርዘው መሆኑን፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይፋ አደረጉ።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሃያ ዓመታት ገደማ ለኖሩና ወደ 262,500 ለሚሆኑ የኤልሳልቫዶር ዜጎች የተሰጠውን ጊዜያዊ ጥበቃና ከለላ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ሊሰርዘው መሆኑን፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ይፋ አደረጉ።

ኤል ሳልቫዶር ውስጥ እአአ በ2001 የደረሰውን ርዕደ ምድር ተከትሎ፣ ከአሜሪካ እንዳይወጡ ለብዙ መቶ ሺህዎች የአገሪቱ ዜጎች የተሰጠው ይህ ጊዜያዊ ጥበቃና ከለላ፣ እአአ በመጪው 2019 መስከረም 9 ቀን እንደሚያበቃ ተገልጧል።

እአአ መስከረም 9/2019 ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለ20 ዓመታት ያህል የኖሩና በህጋዊ መንገድ ሥራ ላይ የነበሩ ከሆኑ፤ የመኖሪያ ፈቃዳቸው ወደ ኢሚግሬሽን ይመራላቸዋል።

ይህ አሁን የተደረሰበት ውሳኔ የብዙዎቹን ህጋዊነት ጥያቄ ላይ ስለሚያስቀምጥ፣ ካገር የመውጣት ዕድልም ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG