በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ2020 የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ የዜግነት ጥያቄን ያካትታል


ፎቶ ፋይል

ቀጣዩ የ2020 የሕዝብ ቆጠራ፣ ለእያንዳንዱ ነዋሪ የሚቀርብ የዜግነት ጥያቄን እንደሚያካትት፣ የዩናይትድ ስቴትሱ የንግድ ሚኒስት ዊልቡረ ሮዝ አስታወቁ።

ቀጣዩ የ2020 የሕዝብ ቆጠራ፣ ለእያንዳንዱ ነዋሪ የሚቀርብ የዜግነት ጥያቄን እንደሚያካትት፣ የዩናይትድ ስቴትሱ የንግድ ሚኒስት ዊልቡረ ሮዝ አስታወቁ።

የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ በየአሥር ዓመቱ በሚያደርገው ጥናት መሠረት ቀጣዩ የሚካሄደው እአአ በ2020 መሆኑም ታውቋል። የሚቀርቡት ጥያቄዎች ተጠናቀው የሚታወቁት በመጪው ቅዳሜ መሆኑም ተገልጧል።

ሚኒስትሩ ሮዝ ትናንት ሰኞ ማምሻው ላይ እንደገለጹት፣ የዜግነት ጥያቄ እንዲጨመር የወሰኑት፥ ከፍትኅ ሚኒስቴር በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት ነው። ይህም፣ የአናሳ ድምፅ ሰጪዎችን የመምረጥ ህግና ሥነ ሥርዓት ለማስከበር እንደሚረዳ ተመልክቷል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ግን፣ የዜግነት ጥያቄው፣ ሰዎች በቆጠራው ከመሳተፍ የሚያግዳቸው ይሆናል በማለት ውሳኔውን ነቅፈዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG