በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቴክሳስ ውስጥ ለጅምላ ጥቃት ሰለባዎች የሻማ ማብራት ስነ ስርዐት ተካሄደ


የአለን፣ ቴክሳስ ፖሊሶች
የአለን፣ ቴክሳስ ፖሊሶች

ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ምዕራባዊዋ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት አለን ከተማ በሚገኝ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ታጣቂ በጅምላ በከፈተው ተኩስ ሰለባዎች የሻማ ማብራት ሥነ ስርዐት ተካሂዷል፡፡

ትናንት ዕሁድ በተካሄደው ሥነ ስርዐት ላይ የከተማዋ ከንቲባ ኬን ፈልክ የከተማ ምክር ቤቱን ወክለው ባደረጉት የማጽናኛ ንግግር “የተፈጸመው አድራጎት ክፉኛ አስደንግጦናል፡፡ የሐዘናችሁ ተካፋይ ነን” ብለዋል፡፡

“ሀዘናችንን ተወጥተን መጽናናታችን አይቀርም፡፡ የአንድ ግለሰብ ድርጊት ያለንን ጽናት እንዲነጥቀን አንፈቅድም፡፡ እንደማህበረሰብ አንድ ላይ ሆነን ከዚህ ሀዘን ይበልጡን በርትተን እንወጣለን፡፡ አሁን ባለንበት የሀዘን ጊዜ ግን ለጥቃቱ ሰለባዎች፡ ለቤተሰቦቻቸው እና ለማህበረሰባችን እንጸልይ” ብለዋል፡፡

ባለስልጣናት እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ ከዳላስ ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው አለን ከተማ አጥቂው “አለን ፕሪሚየም ሞል” ላይ ከሚያሽከረክረው መኪና ላይ ወርዶ በጅምላ ተኩስ በመክፈት ስምንት ሰዎች ገድሏል፡፡ ሌሎች ሰባት ሰዎች ያቆሰለ ሲሆን ከመካከላቸው ሦስቱ በጽኑ መቁሰላቸው ተመልክቷል፡፡ በአካባቢው የነበረ ፖሊስ አጥቂውን ተኩሶ ገድሎታል፡፡

XS
SM
MD
LG