በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ፓኪስታን “ከሽብርተኝነት ጋር ያላት ቁርኝት ዋጋ ያስከፍላታል” አለች


የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን
የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን

"ፓኪስታን ክሽብርተኛነት ጋር ያላት ቁርኝት፣ ዋጋ የሚያስከፍላት ነው" ስትል፣ ዩናይትድ ስቴትስ አስጠነቀቀች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ባወጡት ማስጠንቀቂያ፣ ኢስላማባድ አገሯ ላይ እያየለና እየተበራከተ ከመጣው የሽብርተኛ ቡድን ጋር ያላትን ትሥሥር ካላቆመች፣ ድንበሯን እስከማጣት ያደርሳታል ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ማስጠንቀቂያ ይፋ የሆነው፣ ዋሽንግተንና ኢስላማባድ በመካከላቸው ያለውን አለመተማመን ለማጥበብና፣ ከጎረቤት አፍጋኒስታን ጋርም ሰላም ለመመሥረት ስለሚቻበት ሁኔታ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ትናንት ማክሰኞ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት ነው።

“ከፓኪስታን ጋር በጋራ መሥራት እንሻለን» ሲሉ የተደመጡት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቲለርሰን፣ “ይህ የሚሆነው ግን ፓኪስታን ሃቃኒ ከተሰኘው የሽብርተኛ መረብ ጋር ግንኙነቷን ስታቆም ብቻ ነው” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG