በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ አፕል ኩባኒያ ላይ ክስ መሠረተች


የአፕል አርማ አፕል ምርቶች መሸጫ በብሩክሊን፤ ኒውዮርክ
የአፕል አርማ አፕል ምርቶች መሸጫ በብሩክሊን፤ ኒውዮርክ

የስማርት ስልክ ገበያውን በሞኖፖል ተቆጣጥሯል በሚል፣ የአሜሪካ የፍትሕ መ/ቤት በአፕል ኩባንያ ላይ ዛሬ ሐሙስ ክስ መሥርቷል።

የባይደን አስተዳደር በአይፎን ስልክ አምራች ኩባንያው ላይ የመሠረተው የመጀመሪያውና ከፍተኛው ክስ ነው ተብሏል።

የአሜሪካ መንግሥት ከዚህ ቀደም በጉግል፣ ሜታ እና አማዞን ኩባኒያዎች ላይ ተመሳሳይ ክስ መስርቷል።

ኩባንያዎቹ በአሜሪካ የንግድ ድርጅቶች ሳይመሳጠሩና ገበያውን በብቸኝነት ሳይቆጣጠሩ፣ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ፉክክር እንዲያደርጉ የሚያዘውን “አንቲ ትረስት ሎው” የሚባለውን ሕግ ጥሰዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የአፕል ኩባንያ፣ በገበያ ያለውን የበላይነት በመጠቀም፤ ከአገልግሎት ተጠቃሚዎች፣ ከመተግበሪያ ፈጣሪዎች፣ ከሚዲያ ውጤት አዘጋጆች፣ ከሥነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ አታሚዎች እንዲሁም ከጥቃቅን የንግድ ድርጅቶች ተጨማሪ ገንዘብ ሰብስቧል ሲል የፍትሕ መ/ቤቱ በክሱ ላይ አመልክቷል።

በተጨማሪም አፕል፤ በኮንትራት ግዴታ በማስገባት የስማርት ስልክ ገበያውን በበላይነት ተቆጣጥሯል፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችንም በስልኩ ላይ መድረክ እንዳያገኙ አድርጓል ሲል ክሱ አመልክቷል።

አፕል ከአሜሪካ በተጨማሪ በአውሮፓ፣ ጃፓን እና ኮሪያ ተመሳሳይ ክስ ቀርቦበታል።

ለአፕል እጅግ አትራፊ ከሆነው አሠራሩ ውስጥ አንዱ ፣ የመተግበሪያ ፈጣሪዎችን እስከ 30 በመቶ ኮሚሽን ማስከፈሉ ሲሆን፣ በዚህ ላይ የተመሠረተበት ክስ በአሜሪካ ለረጅም ጊዜ የተጓተተ የፍርድ ሂደት ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። አንድ የፌዴራል ዳኛ፣ ተጠቃሚዎች ኮሚሽን መክፈል ሳያስፈልጋቸው በሌሎች መንገዶች መጠቀም እንዲችሉ አፕል እንዲያመቻች ወስነዋል።

በአውሮፓ ደግሞ፣ ከያዝነው ወር ጀምሮ፣ መተግበሪያ ፈጣሪዎች ለአፕል ኮሚሽን መክፈል ወይም የአፕልን መድረክ መጠቀም ሳያስፈልጋቸው በሌሎች መንገዶች ፈጠራቸውን ለገበያ ማቅረብ እንዲችሉ ተወስኗል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG