በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታይዋኗ ፕሬዚዳንት አሜሪካ ይገኛሉ


የታይዋንን ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ወንን በካሊፎርኒያ ግዛት
የታይዋንን ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ወንን በካሊፎርኒያ ግዛት

የአሜሪካው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ከቪን ማካርቲ በዛሬው ዕለት የታይዋንን ፕሬዚዳንት ሳይ ኢንግ ወንን በካሊፎርኒያ ግዛት አግኝተው የወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሊደረግ የታቀደው ውይይት ከቻይና ተቃውሞ እንዲሁም “የአጠፌታ እርምጃ እንወስዳለን” የሚል ማስፍፈራሪያን አስከትሏል፡፡

ባለፈው ዓመት፣ የታይዋኑ ፕሬዚዳንት፣ የአሜሪካኑ ም/ቤት አፈ ጉባኤ የነበሩትን ናንሲ ፐሎሲ ተቀብለው በማነጋገራራቸው፣ ቻይና በአጠፌታው በአስርት ዓመታት ውስጥ አድርጋ የማታውቀውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ አድርጋለች፡፡

ጓቲማላን እና በሊዝን ጎብኝተው ትናንት ማክሰኞ ካሊፎርኒያ የገቡት ሳይ ከሆቴላቸው ውጪ ደጋፊዎቻቸውና ተቃዋሚዎች ጠብቀዋቸዋል፡፡

ተቃዋሚዎቹ “አንድ ቻይና” የሚል መፈክር ሲያሰሙ፣ ደጋፊዎቻቸው ፎቷቸውንና የአገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ይዘው ታይተዋል፡፡

ታይዋንን እንደግዛቷ የምትቆጥረው ቻይና ሎስ ኤንጀለስ በሚገኘው ቆንስላዋ በኩል ባወጣቸው መግለጫ፣ ሳይ ውይይቱን የሚያደርጉት “ለፖለቲካ ታይታ” ነው ብላለች፡፡

XS
SM
MD
LG