ሶሪያ ጋዜጠኛውን ኦስተን ታይስንም ሆነ ሌላ ማንንም አሜሪካዊ አልጠለፍኩም ብላለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ግን "ጋዜጠኛው በሶሪያ መንግሥት እጅ እንዳለ በእርግጠኛነት እናውቃለን" ሲሉ ከአንድ ሳምንት በፊት መናገራቸው ተዘግቧል።
ኦስተን ታይስ ልክ የዛሬ አሥር ዓመት ነሃሴ ውስጥ ሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ አቅራቢያ ከነበረ አንድ የፍተሻ ኬላ ድብዛው ጠፍቷል።
ታይስ የጠፋበትን አሥረኛ ዓመት ለማሰብ ፕሬዚደንት ባይደን ባወጡት መግለጫ ጋዜጠኛው ወዳገሩ እንዲመለስ ዩናይትድ ስቴትስ የሶሪያን መንግሥት ዕርዳታ በተደጋጋሚ እንደጠየቀች አመልክተዋል።
የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ታይሰን የት እንዳለ እነርሱም እንደማያውቁ ተናግሯል።
በዚያው ዓመት መስከረም ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ፊቱን ሸፍነው ይዘውት ሲሄዱ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሠራጭቶ ነበር።