በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ በሶሪያ ያሉ የኢራን ሸሪክ ኃይሎችን ከአየር ደበደበች


ፎቶ ፋይል፦ የሶሪያ ካርታ
ፎቶ ፋይል፦ የሶሪያ ካርታ

በድጋሚ የታደሰ፦

በምስራቅ ሶሪያ የሚገኙ “ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጓድ ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ሲጠቀሙብት የነበረን አገልግሎት ሰጪ መሰረተ ልማቶችን” ከአየር መደብደቡን የአሜሪካ ጦር ትናንት ማምሻውን አስታውቋል።

ከዩናይትድ ስቴትስ ማዕከላዊ እዝ የኮሚኒኬሽን ሃላፊ ጆ ቡቺኖ የወጣውና ለቪኦኤ የደረሰው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዴር ኤል-ዙር የተደረገውን የአየር ድብደባ ማጽደቃቸውንና፣ ይህም በስፍራው ያሉ የአሜሪካ ኃይሎችን በኢራን ከሚደገፉት ቡድኖች ጥቃት ለመከላከል ነው ብሏል መግለጫው።

“አሜሪካውያንን ለመጠበቅና ለመከላከል የዛሬው ጥቃት አስፈላጊ ነበር። የተጎጂዎችን ቁጥር የቀነሰና ወደተባባሰ ደረጃ የማያደርስ ተመጣጣኝና የታቀደ እርምጃ ዩናይትድ ስቴትስ ወስዳለች” ብለዋል ቡቺኖ።

መግለጫው በተጨማሪም በምስራቅ ሶሪያ የሚገኝ የአሜሪካ ወታደሮችና፣ በአሜሪካ በሚደገፉ የሶሪያ ተቃዋሚ ተዋጊዎች የሚገለገሉበት ቅጥር ግቢ ላይ ነሐሴ 9 ቀን በድሮን የተፈጸመን ጥቃት አስታውሷል።

ኢራን ዛሬ ባወጣችው መግለጫ፣ ሶሪያ ውስጥ በአሜሪካ ዒላማ ከተደረጉት ቡድኖች ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላት አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG