በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ስለ"እስላማዊ መንግሥት" ቡድን ድል መጎናጸፋቸውን ይገልፃሉ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ እራሡን "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" ብሎ በአወጀው በፅንፈኛው ቡድን ላይ ድል መጎናጸፋቸውን በመጪው ሣምንት በይፋ እንደሚያሳውቁ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ትላንት አሸባሪ ቡድኑን ለሚዋጋው ዓለምቀፍ ጥምረት አባላት እዚህ ዋሺንግተን ሲናገሩ፣ "ማንም በዚህ ፍጥነት ይህን ማድረግ ይቻላል ብሎ ያመነ ሰው አልነበረም" ብለዋል።

አሁን ግን ምናልባት በመጪው ሣምንት አንዱን ቀን መቶ በመቶ በነውጠኛው ይዞታ ሥር የሚገኙ ግዛቶችን ስንቆጣጠር ድል በድል መሆናችንን በይፋ ማሳወቅ አለብን ሲሉ አስረድተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያና የደኅንነት ባለሥልጣናት አሁንም ሦሪያ ውስጥ እስከ 1ሺህ 5መቶ የሚደርሱ "እስላማዊ መንግሥት ነኝ" የሚለው ቡድን ተዋጊዎች በ50 ካሬ ኪሎ ሜትር ቦታ ላይ መሽገዋል ብለው ያምናሉ።

የሰሞኑን ከባድ ውጊያ በመጥቀስ ባለሥልጣናቱ የሰጡት ይህ ወታደራዊ ግምጋሜ ከፍተኛ ጥንቃቄ የተመላበት ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG