በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንግሊዝ ከቴክሳሱ እገታ በተያያዘ ሁለት ወጣቶችን አሰረች


ፖሊስ በኮሊቪል፣ ቴክሳስ በሚገኘው የቤተ እስራኤል ምኩራብ ፊት ለፊት።
ፖሊስ በኮሊቪል፣ ቴክሳስ በሚገኘው የቤተ እስራኤል ምኩራብ ፊት ለፊት።

የእንግሊዝ ፖሊሶች ባለፈው ቅዳሜ ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ግዛት ዳላስ ውስጥ በሚገኝ አንድ የአይሁዳውያን ምኩራብ ውስጥ ታገተው ከነበሩ ሰዎች ጋር በተያያዘ ትናንት እሁድ ሁለት ወጣቶችን ይዘው ማሰራቸውን አስታውቁ፡፡

የማንችስተር ፖሊስ ሁለቱን ወጣቶች ያሰረው ከጸረ ሽብር እርምጃ ጋር በተያይዘ መሆኑን ቢገልጽም ክስ የተመሰረተባቸው ስለመሆኑ ወይም ስለክሱም ምንነት አግለጸም፡፡

ያለፈው ቅዳሜ እገታውን የፈጸመው ሰው ወደ ቤተ እስራኤላውያኑ ማምለኪያ በመግባት በቀጥታ ይተላለፍ በነበረው የጸሎት ፕሮግራም ላይ በእስር የምትገኘውን ፓኪስታናዊት ኦፊያ ሰዲቅ እንድትለቀቅ ይጠይቅ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ኦፊያ ሰዲቅ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት የተባለችና አፍጋኒስታን ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን ለመግደል ሞክራለች በሚል እኤአ በ2010፣ 86 ዓመት የተፈረደባት መሆኗ ተነግሯል፡፡

ፓኪስታናዊት የኒዩሮሳይንቲስት ኦፊያ በቴክሳስ ፌደራል እስር ቤት የምትገኝ መሆኑምተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ወደ ምኩራቡ በመግባት 4ቱ ሰዎች ላይእገታውን የፈጸመው ሰው የ44 ዓመቱ ማሊክ ፌይዛል አክራም ሲሆን የእንግሊዝ ዜጋ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ጸጥታ አስከባሪ ኮማንዶዎች ህንጻውን ወረር ፍጻሜው እስኪሆን ድረስ እገታው ለ10 ሰዓታት የቆየ መሆኑ ተነገሯል፡፡

ከምኩራቡ ውስጥ የተኩስ ድምጽና ፍንዳታ ተሰምቶ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን አጋቹ በኤፍቢአይ አባላት መገደሉ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳት ጆ ባይደን ድርጊቱንገና የሚጠራ ቢሆንም የጸጥታ አስከባሪዎች በወሰዱት እምርጃ ታጋቾቹ በሙሉ በመለቀቃቸውና ሁኔታውን በቁጥጥር ስር በማዋላቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ባይደን ማንም ሰው እዚህ አገር ላይ በጥላቻ ተነሳስቶ በተለይ በጸረ ሴማዊነትና አክራሪነት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሁሉ አንታገስም ማለታቸው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG