በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማልያ ጦር የምትሰጠው ድጋፍ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማልያ ጦር የምሰጠውን ድጋፍ በአብዛኛው ልታቆም መሆኑን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ አረጋገጡ። የሙስና መስፋፋትና የተጠያቂነት መጥፋት ናቸው ዋና ዋና ምክንያቶቹ ብለዋል ባለሥልጣናቱ።

ዩናይትድ ስቴትስ ለሶማልያ ጦር የምሰጠውን ድጋፍ በአብዛኛው ልታቆም መሆኑን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለቪኦኤ አረጋገጡ። የሙስና መስፋፋትና የተጠያቂነት መጥፋት ናቸው ዋና ዋና ምክንያቶቹ ብለዋል ባለሥልጣናቱ።

እንደ ምግብ፣ ነዳጅና ጦር መሣሪያዎች ለመሳሰሉ የዩናይትድ ስቴትስ እርዳታዎች፣ የሶማልያ ጦር በቂ የሆነ ተጠያቂነት አለማሳየቱንም እነዚሁ ባለሥልጣት አመልክተዋል።

እርዳታችን ፀረ-ሽብርተኛነትን በመዋጋት ረገድ ካላገለገለና ካልረዳ ድጋፍ ማድረጉ የሚጠቅም አይደለም ሲሉ አንድ ሌላ ባለሥልጣን ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG