በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በትረምፕ ያለመከሰስ መብት ላይ ውሳኔ አሳለፈ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ያለመከሰስ መብት የተገደበ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድቤት ወሰነ።

በርዕዮተ ዓለም አመለካከታቸው የተከፋፈሉት የፍርድቤቱ ዳኞች ስድስት ለሦስት በሆነ ድምፅ ባሳለፉት ውሳኔ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከአራት አመት በፊት የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመቀልበስ አሲረዋል በሚል የተከሰሱበትን የወንጀል ክስ ለታችኛው ፍርድቤት መልሰው ልከዋል።

ፍርድቤቱ በአብላጫ ድምፅ ያሳለፈው ውሳኔ፣ የቀድሞ ፕሬዝዳንቶች በስልጣን ዘመናቸው በተሰጣቸው ኃላፊነት ዝርዝር መሠረት ባከናወኗቸው ተግባራት ሙሉ ለሙሉ ያለመከሰስ መብት እንዳላቸው እና ከተሰጣቸው ኃላፊነት ውጪ ባከናወኗቸው ተግባራት ግን ያለመከሰስ መብታቸው የተገደበ መሆኑን አስታውቋል።

የአሜሪካ የሕግ ሥርዓት ማንም ሰው ከሕግ በላይ አይደለም የሚለውን መሠረት የሚከተል ሲሆን፣ ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ነፃነት እንዳለው እና ማንኛውም ሰው ሕግ ሲተላለፍ ሊከሰስ እንደሚችል ያስቀምጣል።

ፍርድቤቱ ውሳኔ ባሳለፈበት ጉዳይ፣ ትረምፕ ከአራት አመት በፊት የተሸነፉበትን ምርጫ ለመቀልበስ በሞከሩበት ወቅት የውጤቱን ትክክለኛነት ለማስጠበቅ፣ በድምፅ አሰጣጥ እና ቆጠራ ወቅት በተፈጠሩ ችግሮች ተሸንፌያለሁ ከማለት ከማለት ይልቅ አሸንፌያለሁ በማለት የፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደነበር ገልጸው ተከራክረዋል።

ትረምፕ ለሁለተኛ የአራት አመት የስልጣን ዘመን ባደረጉት ምርጫ ተጭበርብሬያለሁ ሲሉ እስካሁን ባቀረቧቸው አምስት ደርዘን የሚጠጉ ክሶች ተሸንፈዋል።

ጠቅላይ ፍርድቤቱ ሰኞ እለት አንድ ፕሬዝዳንት የተጠረጠረበትን የወንጀል ክስ ላይ ተመስርቶ በፕሬዛንቶች ያለመከሰስ መብት ዙሪያ ያሳለፈው ውሳኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን በትረምፕ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሁሉም ፕሬዝዳንቶች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG