በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ፍ/ቤቱ በማኅበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረውን የቴክሳስ ህግ ውድቅ አደረገው


የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትናንት ባስተላለፈው ውሳኔ ትላልቆቹ የማኅበራዊ ሚዲያ ድርጅቶች በሚያስተላለፋቸው ይዘቶች ላይ ቅድመ ምርመራ ወይም ሳንሱር እንዳያደርጉና አንዳንዶቹንም መልእክቶችን በማየት ማገድ እንዳይችሉ የሚከለክለውን የቴክሳስ ህግ ውድቅ ማድረጉ ተመለከተ፡፡

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ፣ ሁለት ትላልቅ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ቡድኖች፣ በሪፐብሊካኑ የተደገፈው ውሳኔ፣ የማኅበራዊ ሚዲያውን መድረክ “ጨርሶ ሊታሰብ የማይችለው ክፉ ነገር ሁሉ ማስተላለፊያ” ሊያደርጉት ይችላሉ በሚል ካቀረቡት መከራከሪያ ጋር የተስማማ ሆኖ መገኝቱም ተመልክቷል፡፡

እገዳው ውድቅ እንዲደረግላቸው ጥያቄ ያቀረቡት ኔት ቾይስ እና ፌስቡክ፣ ትዊተርና ዩቱብ የመሳሰሉትን በአባላት ያቀፈው የኮሚፒውተርና ግንኙነት ኢንደስትሪ ማኅበራት ናቸው፡፡

ጥያቄያቸው 5 ለ 4 በሆነው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ዳኞች ውሳኔ ተቀባይነት ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

የቴክኖሎጂ ድርጅቶቹ ክስ የመሰረቱት በራሳቸው መድረክ ላይ የሚሰጡትን ኤዴቶሪያል ውሳኔ ጨምሮ ህገ መንግሥታዊ የሆነውን የድርጅቶቹን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚገፍ ነው በሚል እገዳውን በመቃወም እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውድቅ የተደረገው ህግ በቴክሳስ ክፍለ ግዛት ህግ አውጭ የሪፐብኪላን አባላት የወጣ ሲሆን በግዛቲቱ አገረ ገዥም የተፈረመበት እንደነበር ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG