በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ጠ/ፍ/ቤት የዩኒቨርስቲዎች ተማሪ አቀባበል መስፈርትና ዘርን ይመለከታል


የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዚህ ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርስቲዎች በሚቀበላቸው ተማሪዎች ማመልከቻ ውስጥ ዘርን እንደ አንድ ወሳኝ መመዘኛ አድርገው መውሰድ መቻል አለመቻላቸውን አስመልክቶ የተነሳውን ክስ የሚመለከት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ እና በኖርዝ ካሮላይና ዩኒቨርስቲ ላይ የተነሱ ክሶችን አጣምሮ የሚመለከት መሆኑን አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በሁሉቱም ክሶች የተነሱትን ጭብጦች ፍርድ ቤቱ ራሱ እኤአ በ2003 ያስተላለፈውና እና በ2016 ደግሞ ያጸናውን እንደሚመለከቱ ገልጿል፡፡

በፍርድ ቤቱ ጸድቆና ጸንቶ የነበረው ህግ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎችን ለመቀበል ዘርን እንደ አንድ መመዘኛ መውሰድ ይችላሉ የሚለውን ህግ የሚመለከቱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ተከራካሪዎች ችሎታና ብቃትን እንጂ ዘርን እንደ መመዘኛ መወሰድ አይገባም የሚል መከራከሪያ ማንሳታቸው ተመልክቷል፡፡

ክሱ መታየት የሚጀምረው በመጭው ህዳር ወር መሆኑም ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG