በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የጠ/ፍ/ቤቱን ጽንስ የማስወረድ ረቂቅ አስተያየት ተቃወሙ


የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

ፕሬዚዳንት ባይደን ከዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሾልኮ ወጥቷል በተባለው ረቂቅ ሰነድ ላይ የተመለከተው የዳኞች አስተያየት እኤአ ከ1973 ጀምሮ ሥራ ላይ የነበረውን ጽንስ የማስወረድ መብትን የሚቀልብስ ነው ሲሉ ተቃወሙ፡፡

ምንም እንኳ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ ባይኖርም የዳኞቹን ውስጣዊ ክርክርና አቋም ይፋ አድርጓል የተባለውና ሾልኮ የወጣው ሰነድ በአገር አቀፍ ደረጃ ክርክር አስነስቷል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ስለዚሁ ሲናገሩ “ከ50 ዓመት በኋላ ወደ ኋላ ተመልሰን ሴት ልጅ የመምረጥ መብት የላትም ስትባል ይህ በትልቁ ያሳስበኛል፡፡ ይህ ማለት የራስና የግል ጉዳይ የሆነውን የሚመለከት ነገር ሁሉ ጥያቄ ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል” ብለዋል፡፡

እኤአ 1973 ጀምሮ ሮቪዌ የሚባል በሚል ስያሜ የሚጠራው ውሳኔ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የጽንስ ማስወረድን የሚፈቅድ ህግ ነው፡፡ ይህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባሉ ሁለቱ ፓርቲዎችና ደጋፊዎች ዘንድ ትልቅ ልዩነትን የፈጠረ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ሲያከራክር የኖረ መሠረታዊ ልዩነት ነው፡፡

በመጭው የምክር ቤት አባላት ምርጫም መራጮችን ሊያነሳሳ ይችላል ተብሎ ተገምቷል፡፡ የውሳኔውን አዝማሚያ ከተሰማ በኋላም በተለያዩ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ ጽንስ ማስወረድ መብት ደጋፊዎች ትናንት ማክሰኞ ባደረጉት ሰልፍ ፍርድ ቤቱ ታሪካዊ ነው የተባለውን ህግ እንዳይቀለብሰው ጠይቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG