በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የተኩስ አቁም ውይይት እንደገና ሊቀጥል ነው ተባለ


ተቋርጦ የነበረውና በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ማቆም ንግግር፣ ነገ ሐሙስ በጀዳ ሳዑዲ አረቢያ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የነገው ውይይት፣ በተለይም በጦርነቱ ምክንያት ችግር ላይ ለውደቁ ሲቪሎች ሰብዓዊ ርዳታ በሚደርስበት ጉዳይ ላይ የሚያተኩር መሆኑን የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መ/ቤት አስታውቋል።

አሜሪካ እና ሳዑዲ አረቢያ ካለፈው ግንቦት ጀምሮ በሱዳን ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል ተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲኖር በርካታ ድርድሮችን ሞክረው ነበር።

አሜሪካ ባለፈው ሰኔ ንግግሩ እንዲቋረጥ ወስና ነበር።

ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸውን በኃይል ለመፍታት በመወሰናቸው እና በመድፍ እና በድሮን ባደረሱት ጥቃት ሲቪሎችን በመጉዳታቸው፣ በሱዳን ከግጭት በኋላ ለሚፈጠረው አስተዳደር ብቁ አይደሉም ሲሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት አሳስበዋል።

የቀጠናው የልማት በይነ መንግስታት፣ ኢጋድ፣ በአዲሱ ድርድር ሚና እንደሚኖረው እና ዋና ፀሓፊው ወርቅነህ ገበየሁ እንደሚገኙም ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG