በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አገሮች ለሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ ተጠየቀ


ፎቶ ፋይል፦ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ
ፎቶ ፋይል፦ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ

“እጅግ ከገነነ ደረጃ እየደረሰ ነው” ሲሉ ያስጠነቀቁት የሱዳን ቀውስ እንዲቆም የተባበሩት አረብ ኢምሬትስን ጨምሮ እገሮች ለሱዳኑ ተፋላሚ ወገኖች የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያቆሙ ስትል ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪ አደረገች።

ከዚህ ቀደም በዳርፉር የደረሰው ፍጅት እጅግ በከፋ መንገድ ራሱን እንዳይደግም”

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ ትላንት ሰኞ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት በአል ፋሺር "መጠነ ሰፊ እልቂት ሊፈጸም ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አምባሳደሯ አክለውም “ከዚህ ቀደም በዳርፉር የደረሰው ፍጅት እጅግ በከፋ መንገድ ራሱን እንዳይደግም” ብለዋል።

የሱዳኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሰሜናዊ ዳርፉር ግዛት አል-ፋሺር ላይ ጥቃት ሊያደርስ ይችላል’ በሚል ያደረበትን ሥጋት የመንግስታት ድርጅት በቅርቡ አስታውቋል።

ከአንድ አመት በፊት በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ተከትሎ በዓለም ግዙፉን የመፈናቀል ቀውስ ማስከተሉ ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG