በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን በተቃዋሚዎች የወሰደችው ዕርምጃና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት ግንኙነት

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሱዳን በመንግሥቱ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየወሰደች ያለችው የኃይል ዕርምጃ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል የተያዙ ጥረቶችን ሊጎዳ ይችላል ሲሉ አንዳንድ ቁልፍ የአሜሪካ ታዛቢዎች አስገነዘቡ።

ሱዳን በመንግሥቱ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ እየወሰደች ያለችው የኃይል ዕርምጃ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል የተያዙ ጥረቶችን ሊጎዳ ይችላል ሲሉ አንዳንድ ቁልፍ የአሜሪካ ታዛቢዎች አስገነዘቡ።

በከፍተኛ ግሽበት በዳቦና በነዳጅ ዘይት ዋጋ መናር ምክንያት - ሕዝባዊ ተቃውሞው ከሁለት ሣምንታት በፊት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችና የአሜሪካ ድምፅን ጨምሮ ሌሎች የዜና ምንጮች፣ ሱዳን ውስጥ ሕገወጥ እሥራት፣ ዕገታና ግድያ መፈፀሙን ዘግበዋል።

የተቃውሞ ሰልፎች ትላንትም ቀጥለው በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች የዋና ከተማይቱ ካርቱምን መንገዶች አጥለቅልቀው የዋሉ ሲሆን - ሃገሪቱን ለረዥም ጊዜ ያስተዳደሩት ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሽር ሥልጣን እንዲለቁ ጠይቀዋል። በሽር ግን ወይ ፍንክች እንዳሉ ነው።

ከቅርብ ቀናት በፊት በታቃዋሚዎች ላይ እየተለሳለሱ የመጡት የሱዳኑ መሪ አብዛኞቹ ተቃዋሚዎች የረባ ምክንያት የሌላቸው ወጣቶች ናቸው፤ ማለታቸውንና ጋዜጠኞችን ለመፍታት ቃል መግባታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG