በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከንና አል ቡርሃን በሱዳን ጦርነት ላይ ተነጋገሩ


ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን በሱዳን በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በሚያበቃበት ጉዳይ ላይ ከሃገሪቱ ሠራዊት አዛዥ አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ጋራ መወያየታቸውን ሚኒስቴር መ/ቤቱ አስታውቋል።

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ማቲው ሚለር እንዳሉት፣ ሁለቱ ወገኖች በሱዳን ያለው ግጭት በአስቸኳይ ቆሞ፣ የሱዳናውያንን ስቃይ ለማቃለል ያልተቋረጠ ሰብዓዊ ድጋፍ በሚደረግበት ላይ ተነጋግረዋል።

ለ30 ደቂቃ በቆየ የስልክ ውይይታቸው፣ በጀዳ ሲካሄድ የነበረው ድርድር እንዲቀጥል እንዲሁም በሰሜን ዳርፉር ባለው ግጭት ሲቪሎች በሚጠበቁበት ላይ ተነጋግረዋል ተብሏል።

በጀዳ ሲካሄድ የነበረው ድርድር ከሶስት ሳምንታት በኋላ እንደሚቀጥል አሜሪካ ባለፈው ወር አስታውቃ ነበር። ትክክለኛው ቀን ግን አልተገለጸም።

አል ፋሸር በተባለችው የሠሜን ዳርፉር ክልል በሁለት ሣምንታት ውስት ብቻ ቢያንስ 134 ሰዎች መገደላቸውን ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን (ኤም ኤስ ኤፍ) አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG