በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችዋን ያቆሰለውን የሚላሻ መሪ ኢራቅ ውስጥ ገደለች


የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ዛሬ ሐሙስ ባግዳድ ውስጥ ባካሄደው የአጸፋ ጥቃት፣ ባላፈው ወር በአሜሪካ ወታደሮች ላይ ለደረሰው ጥቃት ተጠያቂ ነው ያለውን የሚሊሺያ መሪ ገድሏል ሲል፣ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ለሮይተርስ ተናገሩ።

የኢራቅ ፖሊስ ምንጮች እና ምስክሮች አንድ ሰው አልባ አውሮፕላን ቢያንስ ሁለት ሮኬቶችን ምስራቅ ባግዳድ ውስጥ የአል ኑጃባ ሚሊሻዎች በሚጠቀሙባቸው ተቋማት ላይ መተኮሳቸውን ተናግረዋል፡፡

የፖሊስ እና የሚሊሺያ ምንጮች እንዳሉት ሮኬቶቹ በኑጃባ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ የነበረ ተሽከርካሪን በመምታታቸው የአካባቢው የቡድን አዛዥ እና አንድ ረዳታቸውን ጨምሮ አራት ሰዎችን መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

የጤና ምንጮች የሟቾችን ቁጥር ማረጋገጣቸው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የእስራኤል-ሃማስ ጦርነት በጥቅምት ወር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአሜሪካ ጦር ኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ በመደበኛ ሮኬቶች እና በአንድ አቅጣጫ ብቻ በሚያጠቁ ድሮኖች ቢያንስ ለ100 ያህል ጊዜ ጥቃት የደረሰበት መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ 2,500 ወታደሮቿን በኢራቅ እና 900 የሚሆኑትን ደግሞ በጎረቤት ሶርያ በማሰማራት የእስልምና መንግስት አራማጅ ታጣቂዎች ዳግም እንዳያንሰራሩ ለማድረግ እየሞከረች መሆኑ በሮይተርስ ዘገባ ተመልክቷል፡፡

በኢራቅ እና ሶሪያ የሚገኙ ከኢራን የተቆራኙ ቡድኖች እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ዘመቻ በመቃወም ዩናይትድ ስቴትስን በከፊል ተጠያቂ ያደርጋሉ።

“ለዚህ የኢራቅ የጸጥታ አካል ላይ ለተፈፀመው ኢ-ፍትሃዊ ጥቃት፣ የኢራቅ ታጣቂ ኃይሎች ዓለም አቀፍ ጥምር ኃይሎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ” ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ ቃል አቀባይ የዛሬውን ጥቃት በመጥቀስ ተናግረዋል።

መግለጫው የሚሊሺያ ቡድን በጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ ፈቃድ የሚንቀሳቀስ የኢራቅ ጦር ነው ሲል ገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣን በተሽከርካሪው ላይ ጥቃት ያደረሰው የሚሊሻውን መሪ ለመግደል በማሰብ መሆኑን እና ይህም መሳካቱን ተናግሯል።

ባለፈው ወር ከኢራን ጋር የተገናኙ ታጣቂዎች በሰው አልባ አውሮፕላኖች ጥቃት ከተፈፀመ በኋላ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ አገልግሎት አባል በአደገኛ ሁኔታ ላይ ከመድረሱ በኋላ ሁለቱን ቆስለዋል ።

“ለዚህ የኢራቅ የጸጥታ አካል ላይ ለተፈፀመው ኢ-ፍትሃዊ ጥቃት፣ የኢራቅ ታጣቂ ኃይሎች

ዓለም አቀፍ ጥምር ኃይሎችን ተጠያቂ ያደርጋሉ” ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወታደራዊ ቃል አቀባይ የዛሬውን ጥቃት በመጥቀስ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG