በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ተኩስ ስለማቆም ውሳኔ


ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ቢሮ የወጣ ሰኔ 22/2013 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ መንግሥት ትግራይ ውስጥ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጁ ግጭቱ እንዲያበቃ፣ የጭካኔ አድራጎቶች እንዲቆሙና ሰብዓዊ እርዳታ ባልተገደበ ሁኔታ እንዲደርስ ለማስቻል ምድር ላይ ለውጥ ካስገኘ አዎንታዊ እርምጃ ሊሆን ይችላል። ሁኔታዎቹን በቅርብ እየተከታተልን ነን። ሁከቱን ለማክተም፣ ትግራይ ውስጥ መረጋጋት እንዲመለስ ለማድረግና የኢትዮጵያን አንድነት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አሃዳዊነት ማስጠበቅ በሚችል ሁኔታ ሁሉን አቀፍ በሆነ ንግግር አፋጣኝ፣ የጊዜ ገደብ ለሌለውና በድርድር ላይ ለተመሠረተ ተኩስ ማቆም እራሳቸውን እንዲያስገዙ ለሁሉም ወገኖች ጥሪ እናቀርባለን።

ሁሉም ወገኖች ዓለምአቀፍ ሰብዓዊ ህጎችን አጥብቀው እንዲያከብሩና ሰብዓዊ እርዳታ ሳይገደብ እንዲደርስ ለማድረግ እንዲተጉ፤ እንዲሁም ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና ረገጣዎች ተጠያቂነት ነፃ የሆኑ አሠራሮች እንዲዘረጉ እናሳስባለን። የተሳካና ዘላቂ የሆነ ተኩስ ማቆም ላይ ለመድረስ አስፈላጊ የሆነ እርምጃ የኢትዮጵያ መንግሥት መጋቢት ውስጥ በገባው ቃል መሠረት ሁሉም የኤርትራ ኃይሎች በአፋጣኝና ተጣርቶ በሚረጋገጥ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ ጥሪ ማሰማታችንን እንቀጥላለን።

ዋነኛው ቅድሚያችን እጅግ አሳሳቢ ለሆነው ሰብዓዊ ሁኔታ ምላሽ መስጠት ነው። የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እጅግ በበረታ የረሃብ ሁኔታ ውስጥ የሚገኘውን 900 ሺህ ሰው ጨምሮ ህይወት አድን የሆነ የምግብ እርዳታን ለማፋጠን ከኢትዮጵያ መንግሥት፣ ከትግራይ ባለሥልጣናት፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ከሌሎችም ዓለምአቀፍ አጋሮች ጋር ለመሥራት ዝግጁ ነው። ለዚህም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ትግራይ ውስጥ የቴሌኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት በአፋጣኝ እንዲያስጀምሩ፣ የሰብዓዊ ድርጅቶች ሠራተኞች ባልተገደበ ሁኔታ መንቀሳቀስ እንዲችሉ እንዲፈቅዱና ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ እናሳስባለን።

XS
SM
MD
LG