በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከዓለም ህዝብ ገሚሱ ጤናማ ምግብ የመሸመት አቅም የሌለው ነው - አንቶኒዮ ጉቴሬዥ


አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

ትናንት ሃሙስ በተካሄደ የምግብ ጉዳይ የመሪዎች ስብሰባ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ባደረጉት ንግግር ከዓለም ህዝብ ገሚሱ ጤናማ ምግብ የመሸመት አቅም የሌለው ነው ሲሉ አስገነዘቡ።

ዋና ጸሃፊው “ምግብ ማለት ሕይወት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በየቦታው በሃገራት በማኅበረሰቦች እና በመኖሪያዎች ውስጥ ይሄ መሰረታዊ ፍላጎት አልተሟላም” ብለዋል፡፡ የምግብ ጉባዔው በጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን በድረ-ገጽ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጉቴሬዥ ሦስት ቢሊየን የሚሆኑ ሰዎች የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት አይችሉም፥ በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ባዶ ሆዳቸውን ያድራሉ ሕጻናትም እየተራቡ ነው” ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በበየመን ሚሊዮኖች እየተራቡ መሆኑ ዕውነት ሆኖ ሳለ በዓለም ላይ ከሚመረትው ምግብ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው እየወደመ ወይም እየባከነ ነው ሲልም አሳስቧል።

የዓለም የምግብ ጉዳይ የመሪዎች ጉባኤ ከዓየር ንብረት ጋር የሚስማማ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹህና ተደራሽነት ያለው ምግብ ለማድረስ ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰራ ቆይቷል፥ ትኩረቱንም የተመድ ዘላቂነት ያላቸው የልማት ግቦች መሃከል 17ኛ የሆነው ዜሮ ርሃብ ላይ ዕውን ለማድረግ እየሰራ ነው።

XS
SM
MD
LG