ዋሺንግተን ዲሲ —
የደቡብ ሱዳን ፕረዚዳንት ስልቫ ኪርና የተቃዋሚዎች መሪ ሪያክ ማቻር በተስማሙት መሰረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ የሽግግር የውህደት መንግሥት ለመመስረት ባለመቻላቸው “እጅግ ማዘኑን” የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
“ለደቡብ ሱዳን ህዝብ እንዲህ ዓይነቱን መሰረታዊ የሆነ የፖለቲካ ፍላጎት ለማሳያት አለመቻላቸው ራሱ የሀገሪቱን የሰላም ሂደት ለመምራት በመቀጠል ብቃታቸው ላይ ጥያቄ ያስነሳል” ይላል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሞርጋን ኦርታጉስ ያወጡት መግለጫ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ