በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ወደ ፕዮንግያንግ ይጓዛሉ


የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ስቴፈን ቢገን
የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ ስቴፈን ቢገን

በፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕና በሰሜው ኮርያው ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኡን መካከል የሚካሄደውን የሁለተኛ ዙር ውይይት ዝግጅት ለማጠናቀቅ፣ የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ በዚህ ሳምንት ወደ ፕዮንግያንግ እንደሚጓዙ ተገለፀ።

የዩናይትድ ስቴትሱ የሰሜን ኮሪያ ልዩ መልዕክተኛ በዚህ ሳምንት ወደ ፕዮንግያንግ እንደሚጓዙ ሲገልፅ፣ ልዩ መልዕክተኛው ስቴፈን ቢገን ከሰሜን ኮሪያ አቻቸው ኪም ሀይክ ቾል ጋር ነገ ረቡዕ ይገናኙሉ፣ ባለፈው ሰኔ ወር ሁለቱ መሪዎች ሲንጋፖር ውስጥ ባካሄዱት አንደኛ ዙር ውይይት የተገኘውን ውጤት እንደሚገመግሙና በቀጣይነቱም ላይ እንደሚነጋገሩ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ባለፈው ዕሑድ ሶል ደቡብ ኮሪያ ከገቡት ዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ ልዑክ ከዚያው ከሶል ነው ወደ ፕዮንግያንግ ይጓዛሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG