በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሰሜን ኮሪያው ስጋት ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ የጦር ልምምዶቻቸውን እያሳደጉ ነው


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተንና የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ሊ ጆንግ ሱፕ
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተንና የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ሊ ጆንግ ሱፕ

ዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ፣ የሰላምና የጋራ ወታደራዊ ልምምዶቻቸውን የሚያካሂዱባቸውን መስኮች በማስፋት፣ ከሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የሚካሄዱ የሚሳዬል ሙከራዎችን አስመልክቶ፣ የመረጃ ልውውጦቻቸውን እንደሚያሳድጉ ዛሬ አስታወቁ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተንና የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስትር ሊ ጆንግ ሱፕ፣ ባላፈው ዓመት ውስጥ ባልተመደ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል ላሉት የሰሜን ኮሪያ ትንኮሳ ተጨማሪና ቆራጥ ምላሾችን እንደሚሰጡ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቃል ገብተዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሶል፣ በአገሪቱ የመከላከያ ጽ/ቤት ውስጥ በሰጡት መግለጫ ዋሽንግተን የረጅም ጊዜ አጋሯን ለመመከት ፔንታገን “መደበኛውን ጦር ኒውክለር እና የሚሳዬል መከላከያዎችን ሁሉ ጨምሮ፣ የዩናይትድ ስቴትስን ሙሉ የመከላከያ አቅም” ይጠቀማል” ሲሉ ለደቡብ ኮሪያ ባለሥልጣናት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ከመደበኛው ወታደራዊ ልምምዶች በተጨማሪ፣ ከፍተኛና ልዩ ወታደራዊ የጦር ልምምዶችን እንደሚያካሂዱ፣ ሁለቱ የመከላከያ ሚኒስትሮች ኦስትን እና ሊ ጨምረው መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ኮሪያ ውስጥ የሰፈሩ 28,500 ወታደሮች እንዳሏት በዘገባው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG