በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የአል-ሻባብን የገንዘብ ምንጭ ለማድረቅ እየሠራች ነው


ፎቶ ፋይል፦ የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት ያደረሱበት ስፍራ ነዋሪዎች ውድመቱን እየተመለኩ፣ ሞቃዲሾ፤ ሶማሊያ እአአ 08/21/2022
ፎቶ ፋይል፦ የአልሸባብ ታጣቂዎች ጥቃት ያደረሱበት ስፍራ ነዋሪዎች ውድመቱን እየተመለኩ፣ ሞቃዲሾ፤ ሶማሊያ እአአ 08/21/2022

ዩናይትድ ስቴትስ መጠነ ሰፊ ተጨማሪ ማዕቀቦችን፣ የድሮን ጥቃትና በውጊያ ዘመቻው እየተሳተፉ ላሉ አጋሮቻቸው ወታደራዊ መረጃዎችን እና ምክር መስጠትን ጨምሮ የአል-ቃይዳ ሸሪክ በሆነው አል-ሻባብ ላይ የምታደርገውን ዘመቻ አጠናክራ ቀጥላለች።

በተጨማሪም የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በአራት የአል-ሻባብ መሪዎች እና ለቡድኑ ገንዘብ በማሰባሰብ፣ ተዋጊዎችን በመመልምል እና መሣሪያ በማፈላለግ ሥራ ቁልፍ ተዋናዮች ናቸው ባሏቸው አስር አቀነባባሪዎቻቸው ላይ የተነጣጠረ ማዕቀብ ይፋ ጥሏል።

ግለሰቦቹ ዩናይትድ ስቴትስ እንደምትለው ሕገ-ወጥ መዋቅሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ምንጮች በዓመት በ100 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ለቡድኑ ይሰበስባል።

ሂራል ኢንስቲቱት በተባለ በሞቃዲሹ መሠረቱን ባደረገ ተቋም በቅርቡ የወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው ወደ 24 ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ለመሣሪያ ግዢ የሚውል ነው። ይህን ግምት የተመድ አባል አገራት ባላቸው የመረጃ ግንኙነት እንዳረጋገጡት ታውቋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ይፋ ያደገችው አዲስ ማዕቀብ ባለፈው ሳምንት የሶማሊያ መንግስት በአልሸባብ ላይ ያወጣውን አዲስ ሕግ ተከትሎ የመጣ ነው። ለአል-ሸባብ ገንዘብ የሚያዋጡ ነጋዴዎች ፈቃዳቸው ተነጥቆ ንብረታቸው እንደሚወረስ መንግስት ደንግጎ ነበር።

በተማሪም ባለፈው ሳምንት፣ ሶማሊያ አል-ሸባብን በተሻለ መሣሪያ ለመፋለም በተመድ የተጣለባትን የመሣሪያ ግዚ ማዕቀብ ለማስነሳት በምታደርገው ጥረት ከኢትዮጵያ ድጋፍ አግኝታለች።

XS
SM
MD
LG