በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊያ በኮሎኔልነት ያገለገሉት ግለሰብ በዩናይትድ ስቴትስ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ ተፈረደባቸው


ዩሱፍ አብዲ አሊ በቀድሞው የሶማሊያ ዚያድባሬ ዘመን ኮሎኔል
ዩሱፍ አብዲ አሊ በቀድሞው የሶማሊያ ዚያድባሬ ዘመን ኮሎኔል

ከበርካታ ዓመታት በፊት በሶማሊያ ብሄራዊ የጦር ሰራዊት ውስጥ በኮሎኔልነት ያገለገሉ አንድ ሰው እኤአ በ1987 በአንድ ታዳጊ ወጣት ላይ የማሰቃየት ተግባር በመፈፀም በዩናይድት ስቴትስ ፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ብይን ተሰጥቷቸዋል።

በአሁኑ ጊዜ ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂኒያ ክፍለ ሀገር አሌክሳንድሪያ ውስጥ የሚኖሩት ዩሱፍ አብዲ አሊ በቀድሞው የሶማሊያ አምባገነን በዚያድባሬ ዘመን ኮሎኔል የነበሩ መሆናቸው ተመልክቷል። በወረዳው ያስቻለው ከህዝብ የተውጣጣ ክስ ሰሚ ችሎት ተከሳሹ ፋርሃን መሃመድ ታኒ ዋርፋ የተበለው ግለሰብ ላይ ለተደረሰው ሰቆቃ ተጠያቂ ናቸው ብሎ ለፋርሃን አምስት መቶ ሺህ ዶላር እንዲከፍሉ ወስኗል።

በቀድሞው ኮሎኔል ላይ ክሱን ፋርሃን ዋርፋን ወክሎ ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት የመሰረተው ጽህፈት ቤቱ ሳን ፍራንሲስስኮ የሆነው የፍትህና የተጠያቂነት ማዕከል የተባለ ተቋም ሲሆን ክስ ሰሚው የህዝብ ሸንጎ ለሦስት ቀናት ከተነጋገረበት በኋላ ነው የጥፋተኝነት ውሳኔ የሰጠው።

በወቅቱ የአስራ ሰባት ዓመት ወጣት የነበረው ዋርፋ ኮሎኔሉ

“እአአ በ1988 ሲመረምሩኝ፣ ስያሰቃዩኝ ቆይተው በጥይት መተውኝ ሞቷል ብለው ጥለውኝ ሄዱ። ቅበሩት ለተባሉት ሰዎች ግንዘብ ከፍዬ ተረፍኩ” ብሏል።

ትናንት የቅጣት ውሳኔውን የሰጡት ከህዝብ የተውጣጡ ዳኞች በዋርፋ ላይ ለደረሰው ሰቆቃ ተከሳሹን ተጠያቂ አድርጎ የተኮሱበት ሆን ብለው ለመግደል ለመሆኑ ግን በቂ ማስረጃ አላገኘንም ብለዋል።

ከሳሹ ዋርፋ በአሁኑ ወቅት የሚኖረው ሰሜናዊ ሶማሊያ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG