ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ደኅንነት ሚኒስቴር ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚገኙ ጥገኝነት የጠየቁ ቁጥራቸው ወደ አምስት መቶ ለሚጠጋ ሶማሊያውያን የተሰጣቸውን ጊዚያዊ ህጋዊ ከለላ እንዲራዘምላቸው ወሰነ።
የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ደኅንነት ሚኒስትር ኪርስቲን ኔልሰን ሶማሊያ ውስጥ የቀጠለው የትጥቅ ግጭት ልዩ የሆነ ሁኔታ በእንግሊዝኛ አህጽሮት /ቲፒኤስ/ ተብሎ በሚጠራው የጊዚያዊ ከለላ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ መቆየቷን አስፈላጊ ያደርገዋል ብለዋል።
ዘላቂ መፍትኄ መፈለግ ይኖርብናል ያሉት ሚኒስትሩዋ ያ ካልሆነ ግን ሁከት እና የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሸሽተው መጥተው ይህችን ሀገር ሃገሬ ብለው የሚኖሩ በመቶዎች የተቆጠሩ ሶማሊያውያን ጎረቤቶቻችን የመባረር አደጋ ይደቀንባቸዋል ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ