በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከፍተኛ የአል-ሻባብ አዛዥ በአሜሪካ እና ሶማሊያ የጋራ ዘመቻ ተገደለ


ጂሊብ፣ ሶማሊያ
ጂሊብ፣ ሶማሊያ

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ፣ ጂሊብ በተሰኘች ከተማ አቅራቢያ ባካሔደችው የአየር ጥቃት፣ አንድ ከፍተኛ የታጣቂ ቡድኑ አዛዥ እንደተገደለ፣ የሶማሊያ መንግሥት አስታወቀ።

ማሊም አይማን የተባለው አዛዡ፣ የአል-ሻባብ ታጣቂ ቡድን፣ በሶማሊያ እና በኬንያ ባካሔዳቸው ጥቃቶች ውስጥ ተሳታፊ እንደነበር ሲታወቅ፣ በሶማሊያ ጦር ኀይሎች እና በዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች በተወሰደ የትብብር ርምጃ እንደተገደለ፣ የሶማሊያ መንግሥት ጨምሮ ገልጿል።

የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስትር፣ ትላንት ኀሙስ ባወጣው መግለጫ፣ “ከሶማሊያ ሕዝብ ላይ አንድ እሾኽ መነቀል ማለት ነው፤” ሲል ግዳዩን አወድሷል።

የዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ ጦር(አፍሪኮም) በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፣ በጂሊብ አጠገብ በተሰነዘረው ማጥቃት፣ አንድ የአል-ሻባብ ታጣቂ መገደሉን አረጋግጦ፣ በሲቪሎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጧል። የተገደለውን ታጣቂ ማንነት በስም ያልጠቀሰው የአፍሪኮም መግለጫ፣ “የሶማሊያን ሰላም እና ልማት የሚያናጋውን አሸባሪ ቡድን በማሸነፍ ረገድ አንድ ሌላ ርምጃ ነው፤” ሲል አመልክቷል።

መግለጫው አክሎም፣ “አፍሪኮም፣ የተካሔደውን ወታደራዊ ዘመቻ መርምሮ እንዳስፈላጊነቱ ተጨማሪ መረጃዎችን ያቀርባል፤” በማለት ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

አል-ሻባብ ግን፣ እስከ አኹን ግድያውን አስመልክቶ የሰጠው መረጃ የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG