በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮርያ ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር ኮሮናቫይረስ መያዙ ተገለፀ


ደቡብ ኮርያ ውስጥ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደር ኮሮናቫይረስ እንደያዘው የአሜሪካ ወታደራዊ ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።

የ23 ዓመት ዕድሜ ወጣት የሆነው በሽተኛ ከወታደራዊው ሰፈር ውጭ በሆነው መኖርያ ቤቱ ተወስኖ እንደሚገኝ ደቡብ ኮርያ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ባወጣው መገልጫ ገልጿል።

ሌሎች ለበሽታው የተጋለጡ ሰዎች ካሉ ለማጣራት ሲሉ የጤና ባለሙያዎች ከወታደሩ ጋር የተገናኙ ካሉ እየተከታተሉ መሆናቸውን ደቡብ ኮርያ ያለው የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል ያወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

ወታደሩ ካምፕ ካሮል በተባለው በሀገሪቱ ደቡብ ምስራቅ ክፍል በሚገኝ የዩናይተድ ስቴትስ ወታደራዊ ሰፈር ነበር የተመደበው።

“ካምፕ ወልከር” በተባለው ወታደራዊ ሰፈርም ደርሶ እንደነበር ታውቋል።

ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሰፈሮች ደቡብ ኮርያ ውስጥ ኮሮናቫይረስ በገባበት ሰፈር አጠገብ መሆናቸው ተገልጿል።

ደቡብ ኮርያ ውስጥ ዛሬ 169 አዲስ የኮሮናቫይረስ በሽተኞች እንደተገኙ ባለሥልጣኖች ገልፀዋል። በአጠቃላይ 1,146 በሽተኞች እንዳሉ ተረጋግጧል። ባለፈው ሳምንት 30 በሽተኞች እንደነበሩ ነበር የተገለፀው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG