በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ የደነገገችው የገቢ ሸቀጥ ቀረጥ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል

U.S. President Donald Trump is after signing a proclamation to establish tariffs on imports of steel and aluminum at the White House in Washington, March 8, 2018.
U.S. President Donald Trump is after signing a proclamation to establish tariffs on imports of steel and aluminum at the White House in Washington, March 8, 2018.

ዩናይትድ ስቴትስ ከአውሮፓ ህብረት ከካናዳና ከሜክሲኮ ወደሃገርዋ በሚገባ ብረት የሃያ አምስት ከመቶ እና አልሙኒየም ላይ ደግሞ አሥር ከመቶ ቀረጥ በመጣል የአትላንቲክ ተሻጋሪና ሰሜን አሜሪካ ንግድ ግንኙነቶች ውጥረቱን እያባባሰች ናት።

ዩናይትድ ስቴትስ ከአውሮፓ ህብረት ከካናዳና ከሜክሲኮ ወደሃገርዋ በሚገባ ብረት የሃያ አምስት ከመቶ እና አልሙኒየም ላይ ደግሞ አሥር ከመቶ ቀረጥ በመጣል የአትላንቲክ ተሻጋሪና ሰሜን አሜሪካ ንግድ ግንኙነቶች ውጥረቱን እያባባሰች ናት።

አሜሪካ የደነገገችው ከባድ የገቢ ሸቀጥ ቀረጥ ከነገ ዓርብ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

ዕርምጃው ከአውሮፓ ሃገሮች በኩል ፈጥኖ የአፀፋ ዕርምጃ የቀሰቀሰ ሲሆን ሃርሊ ዴድሰን ሞተር ብስኪሌቶች፣ ሊቫይስ ጂንስ ልብሶች፣ የኬንተኪ አረቄ እና የቴኒሲ ውስኪ በመሳሰሉት ታዋቂዎቹ ምርቶች ላይ ሳያነጣጥር እንደማይቀር ይጠበቃል።

የዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ሚኒስትር ዊልበር ሮስ በሰጡት ቃል መፈታት ያለባቸው ሊሎችም ጉዳዮች ስላሉ ባንድ ወገን ከሜክሲኮና ከካናዳ በሌላ ወገን ደግሞ ከአውሮፓ ኮሚሽን ጋር ድርድራችንን ለመቀጠል እንፈልጋለን ብለዋል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ዣን ክሎድ ዩንከር በበኩላቸው በሰጡት ምላሽ ይሄ ለዓለም ንግድ መጥፎ ቀን ነው ካሉ በኋላ በዓለምቀፍ የንግድ ድርጅት አቤቱታ አስገብቶ ከመሟገትና በአሜሪካ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ቀረጥ ከመጣል ሌላ አማራጭ የለንም ብለዋል።

ዓለምቀፍ የንግድ ህግጋትን እያከበርን የአውሮፓ ሕብረትን ጥቅሞች ከማስጠበቅ አንቦዝንም ሲሉም ዩንከር አስታውቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እስካሁን የሚሰራባቸው የንግድ ውሎች የሀገራችንን ኩባኒያዎች የሚጎዱ እና አሚሪካውያንን የሥራ ዕድል የሚያሳጡ በመሆናቸው የተጣለው ቀረጥ ለአሜሪካ ብሄራዊ ፀጥታ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ቆይተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG