በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ከፊል የመንግሥት ሥር ከተዘጋ 17ኛ ቀኑን ይዟል


የዩናይትድ ስቴትስ ከፊል የመንግሥት ሥር ከተዘጋ ዛሬ 17ኛ ቀኑን ይዟል።

የዩናይትድ ስቴትስ ከፊል የመንግሥት ሥር ከተዘጋ ዛሬ 17ኛ ቀኑን ይዟል። ፕሬዚዳንት ዶናል ድትረምፕ ከሜርክሲኮ ጋር በሚዋሰነው ድንበር ላይ ግንብ ለመገንባት የሚያስፈልግ ባጀት እንዲመደብ በሚለው አቋማቸው ጸንተዋል። የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዲሞክራቶች ደግሞ የተዘጉት መሥሪያ ቤቶች እንዲከፈቱ ሊረዳ በሚችል ዕቅደ-ሃሳብ ላይ ድምፅ ለመስጠት እየተዘጋጁ ናቸው።

አዲስ የሥራ ሳምንት በተጀመበት በዛሬው ዕለት በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሥራተኞችሥራ መግባት አይችሉም። ሌሎች በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግሥት ሠራተኞች ደግሞ የሚከፈላቸው መቼ እንደሆነ ባይውቁም በሥራ ገበታቸው ተገኝተው እየሰሩ ናቸው።

የህግ መምርያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የተዘጉት መሥሪያ ቤቶች እንዲካፈቱ በነፍስ ወከፍ መሥሪያ ቤቶች ባጀት ላይ ድምፅ እንዲሰጥበት አደርጋለሁ ብለዋል። ቅድሚያ የሚሰጣቸው የገንዘብ ሚኒስቴርና የሀገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት እንደሚሆኑ ገልፀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG