በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል መ/ቤቶች በከፊል ከተዘጉ 24ኛ ቀን ሆነ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በከፊል የተዘጉት የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ዛሬ 24ኛ ቀናቸውን ያዙ፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና ተቃዋሚዎቻቸው ዴሞክራቶችም፣ ፕሬዚዳንቱ የጠየቁትን የአጥር መገንቢያ ወጪ ላለመፍቀድ እንደተፋጠጡ ናቸው።

በከፊል የተዘጉት የዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል መሥሪያ ቤቶች ዛሬ 24ኛ ቀናቸውን ያዙ፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና ተቃዋሚዎቻቸው ዴሞክራቶችም፣ ፕሬዚዳንቱ የጠየቁትን የአጥር መገንቢያ ወጪ ላለመፍቀድ እንደተፋጠጡ ናቸው።

«በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት (ቅዳሜና እሑድ) ጠበቅኋቸው፣ እነርሱ ግን ነገሬም አላሉት» ሲሉ ትረምፕ በትዊተር ገልፀዋል።

"ቢፈልጉ ኖሮ የምክር ቤት ዴሞክራት መሪዎች፣ አፈ-ጉባዔዋ ናንሲ ፔሎሲና በሴኔቱ አነስተኛ ቁጥር መቀመጫ ያሏቸው አባላት መሪው ቸክ ሹመር የተዘጉትን መሥሪያ ቤቶች በ15 ደቂቃ ሊከፍቷቸው ይችሉ ነበር - የዴሞክራቶች ጥፋት ነው" ብለዋል ትረምፕ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሁኑ ሰዓት 800,000 የፌዴራል መሥርያ ቤት ሠራተኞች ወይ ሥራ ላይ አይደሉም ፤ አልያም ያለ ክፍያ እየሠሩ ናቸው።

መሥራያ ቤቶቹ ሲከፈቱ ግን ያልተከፈላቸው ሠራተኞች ወዲያውኑ ክፍያቸው እንደሚፈቀድ ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ውሳኔ ላይ መድረሱ አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG