በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለኢትዮጵያ ለገሰች

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ 1,680,120 የኮቪድ-19 የፋይዘር ክትባት መድሃኒቶችን ለገሰች። እአአ ጥር 24 እና 26/2022፣ 840ሺ 060 የሚሆነው ዶዝ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሰዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ 1,680,120 የኮቪድ-19 የፋይዘር ክትባት መድሃኒቶችን ለገሰች። እአአ ጥር 24 እና 26/2022፣ 840ሺ 060 የሚሆነው ዶዝ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሰዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ 1,680,120 የኮቪድ-19 የፋይዘር ክትባት መድሃኒቶችን መለገሷን በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

በዓለም አቀፉ የክትባት ስርጭት ማስተባበሪያ ኮቫክስ አማካይነት የተላከው የክትባት መድሃኒት ህይወት የማዳን ዓላማን መሰረት በማድረግ ብቻ የተሰጠ መሆኑንም ኤምባሲው አመልክቷል፡፡

በሁለት ዙር ከተላከው የክትባት መድሃኒት ውስጥ 840ሺ 060 የሚሆነው ባላፈው ሰኞ ጥር 24 አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ መድረሱ በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

ይህ እኤአ ከሐምሌ 17 2021 ጀምሮ ከአሜሪካ ህዝብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሰጠውን የክትባት መድሃኒት ቁጥር 6.1 ሚሊዮን በላይ እንደሚያደርሰውም ኤምባሲው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG