በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ተመድ የሰብአዊ ምክር ቤት አባልነት ልትመለስ ነው


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ በኒው ዮርክ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ በኒው ዮርክ

ዩናይትድ ስቴትስ እኤአ በ2018 በትራምፕ አስተዳደር ትታው ወደ ወጣችውና አወዛጋቢ ወደ ሆነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰአብአዊ መብት ምክር ቤት ተመልሳ ለመግባት ዝግጅት እያደረገች ነው፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት ምክር ቤት ዛሬ ሀሙስ፣ 47 አገሮች አባል ወደ ሆኑበት ጉባኤ፣ ለመግባት በታጩ 18 አዲስ አባል አገሮች ላይ ድምጽ ይሰጣል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ከእነዚህ አገሮች መካከል አንዷ ስትሆን፣ በምክር ቤት ያለውን መቀመጫ ለማግኘት፣ የአብላጫውን ድምጽ ብቻ ማግኘት ይበቃታል፡፡

ይሁን እንጂ ፣ ከአዳዲሶቹ አገራት ውስጥ የቀረበ ምንም ተቃውሞ ስለሌለ፣ ሁሉም ወደ ምክር ቤቱ አባልነት ይቀላቀላሉ የሚል ግምት አሳድሯል፡፡

ከአዳዲሶቹ አገራት መካከል አርጀንቲና፣ ህንድ፣ ሉቲዊያና ኳታር እና ሶማልያ ይገኙበታል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ምክር ቤት ድሬክተር ሉዊስ ሻርቦናው “በመንግሥታቱ የሰብአዊ ድርጅት የሚካሄደው ምርጫ፣ በዓለም ምርጫ ላይ የሚደረግ ቀልድ ነው” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG