በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉዲፈቻ ሐላፊነት በሚሰማቸው ድርጅቶች እንደ መጨረሻ አማራጭ እንዲከናወን አሜሪካዊቷ ሴናተር ጠየቁ


ሴናተር ላንድሩ ህጻናትን ሲጎበኙ
ሴናተር ላንድሩ ህጻናትን ሲጎበኙ

ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናትን ከማሳደግ አንፃር አለም አቀፍ ጉዲፈቻ፤ የመጨረሻ አማራጭ እንደሆነ የአሜሪካ ሴናተር ሜሪ ላንድሩ አስታወቁ፡፡ ባለፈው አመት ብቻ ከ 2100 በላይ ኢትዮጵውያን ህጻናት በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ ሄደዋል፡፡

ባልቻ አባ ነፍሶ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የተሰራው በአሜሪካው ባክነር ኢንተርናሽናል የገንዘብ ድጋፍና፤ በኢትዮጵውያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ‹ብሩህ ተስፋ› አስተባባሪነት ነው፡፡

ከ2 አመት በፊት የተቋቋመው ይኸው ት/ቤት አቅም የሌላቸውን ወላጆች ለመርዳት ታስቦ ነው፡፡

ሴናተር ላንድሩ ካአደጉ አገሮች ለሚመጡ ወላጆች ህጻናትን በጉዲፈቻ የመስጠት አሰራር ሃላፊነት ባለው መልኩ መከናወን እንደሚገባው ተናግረዋል።

“የአሜሪካውያንና የሌሎችም የዓለም ሀገሮች ፍላጎት ዓለም አቀፉን ስምምነት መከተል ነው። ስምምነቱ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር መቆየት እንዳለባቸው ይናገራል፣” ብለዋል።

“ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ያን ህጻን መደገፍ ያለበት በዚያው በቤተሰቡ ውስጥ ነው። የሆነ ነገር ተፈጥሮ ህጻኑ በሞትም ይሁን በረሃብ ወይም በበሽታ ሳቢያ ከናት ወይ ካባቱ ከተነጠለ ፈቃደኛ የቅርብ ዘመድ ጋር መቀመጥ እንዳለበት ስምምነቱ ይናገራል።”

ይሄ ካልተሳካ ግን “በሀገር ውስጥ ሌላ ቦታ መፈለግ ነው” ብለዋል ሴናተር ላንድሩ። “እንደመጨረሻ አማራጭ ህጻናቱን ጎዳና ላይ ወይም ፍቅር የማያገኙበት ተቋም ውስጥ ከማስቀመጥ ይልቅ ከዓለም አካባቢ ቤተሰብ መፈለግ ይገባል።”

XS
SM
MD
LG