በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አንጋፋ አባል ጠየቁ


ሴናተር ቤን ካርዲን
ሴናተር ቤን ካርዲን

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ አንጋፋ አባል ሴናተር ቤን ካርዲን ናቸው፤ በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የታሰሩት የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎችና ጋዜጠኞች እንዲለቀቁ የጠየቁበትን ጋዜጣዊ መግለጫ ያወጡት።

የምክር ቤት አባሉ አክለውም፤ የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችን፥ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትንና የሲቪል ማኅበረሰብ ታጋዮችንም እንዲፈታ፣ የፖለቲካ ምሕዳሩን ለማስፋት የሚያስችሉ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስድና እንዲሁም በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎትና አቅርቦቶች ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ፤ ሲሉ ጠይቀዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በጠራውና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ ላይ ትኩረት ያደረገ ሥነ ሥርዓት የምስክርነት ቃል ከሰጡ በኋላ ባለፈው ሳምንት ወደ አገራቸው ሲመለሱ መታሰራቸውን የገለጸው የሴናተር ካርዲን ጋዜጣዊ መግለጫ “የዶ/ር መረራ ጉዲና እስር በመንግስቱ ላይ የሰላ ትችት የሚሰነዝሩ የፖሊቲካ ተቃዋሚ በመሆናቸው ብቻ ነው። በመሆኑም በአስቸኳይ መለቀቅ አለባቸው” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አንጋፋ አባል ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:13 0:00

XS
SM
MD
LG