በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር በታላቁ ኅዳሴ ጉዳይ


ፎቶ ፋይል

የትረምፕ አስተዳደር ስለኢትዮጵያው ታላቁ የኅዳሴ ግድብ ለመነጋገር የኢትዮጵያን፣ የግብጽንና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እንደጋበዘ ተዘግቧል። በኢትዮጵያና በካይሮ መካከል ያለውን ውጥረት ለማርገብ ነው ተብሏል።

በአሜሪካ ድምጽ እጅ የገባውን የጥሪ ደብባቤ ለሦስቱ ሀገሮችና ለዓለም ባንክ ፕረዚዳንት ዴቪድ ማልፓስ ባለፈው ሰኞ የላኩት የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር ሚኒስትር ስቲቭን ምኑቺን ናቸው።

የዓለም ባንኩ ፕረዚዳንት ሦስቱ ሃገሮች ተገኝተው ሙሉ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ በመገመት በስብሰባው እገኛለሁ ማለታቸውን ቃል አቀባያቸው ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ እና የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ አልሲሲ
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ እና የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ አልሲሲ

በግደቡ ጉድይ የውጭ ሸምጋዮች እንዲገቡ ስትጠይቅ የቆየችው ግብጽ በመጪው ህዳር ወር በምኑቺን መሥሪያ ቤት እንዲካሄድ በታቀደው ስብሰባ እንደምትገኝ ገልፃለች።

የግብጽ ፕረዚዳንት ዐብደል ፋታሕ ኤል-ሲሲ ባለፈው መስከረም ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን በሚመለከት የተከሰተውን ችግር ለመፍታት በሽምግልና እንዲገቡ ፕረዚዳንት ትረምፕን ጠይቀው እንደነበር አንድ ከፍተኛ የትረምፕ አስተዳደር ባለሥልጣን አረጋግጠዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG