በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክ ፖምፔዎና ንጉስ ሳልማን በኢራን ጉዳይ ተወያዩ


ማይክ ፖምፔዎ እና የሳኡዲው ንጉስ ሳልማን
ማይክ ፖምፔዎ እና የሳኡዲው ንጉስ ሳልማን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ እና የሳኡዲው ንጉስ ሳልማን ኢራን ስለደቀነቻቸው የጸጥታ ችግሮች ዛሬ ሪያድ ውስጥ ተወያይተዋል።

ማይክ ፖምፔዎ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ከኢራን ጋር ለመደራደር ዝግጁ እንደሆኑ ገልጸው፣ ነገር ግን ከዚያች ሃገር መሪዎች ጋር ድርድር ጠረጰዛ ለመቀመጥ አልቸኩልም ማለታቸው ተጠቅሷል።

ዩናይትድ ስቴትስ የኢራንን የኒውክሊየር መርሃ ግብር ከሚመለከተው ዓለምቀፍ ሥምምነት ከወጣች ወዲህ የሁለቱ ሃገሮች ውጥረት እየተባባሰ መጥቷል።

ባለፈው ዓመት ኢራን የፈፀመችው ነው በተባለ ጥቃት የሳውዲ የነዳጅ ዘይት ጣቢያዎች ከተመቱ በኋላ ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ወታደሮች ወደ ሳኡዲ ልካለች። ቴህራን በጥቃቱ እጄ የለበትም ስትል ውንጀላውን አስተባብላለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ ወደፊት ምንም ዓይነት ጥቃት ቢቃጣ ለመከላከል የሚሳይል መከላከያ እና ተዋጊ ጄቶች መላኳን አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ፖምፔዎ በሦስት ቀናቱ የሳውዲ ጉብኝታቸው ከመሪዎቹ ጋር በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም በሳውዲ መንግሥት ተከሶ ካገር እንዳይወጣ ተከልክሎ ስላለው ሳኡዲያዊ አሜሪካሲ ሃኪም ለመወያየት ዕቅድ መያዛቸውን ገልጸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG