በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዝዳንት ባይደን በመካከለኛው ምሥራቅ ከሚያደርጉት ጉብኝት ጋር ለተያያዘ ዲፕሎማሲያዊ ሥራ ብሊንከን ዮርዳኖስ ገቡ


የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን
የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ዮርዳኖስ የሚያደርጉትን ጉብኝት ከመጀመራቸው አስቀድሞ ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ለማካሄድ ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ላይ አማን ገብተዋል።

በእስራኤል እና በሃማስ መካከል የተጀመረው ጦርነት ወደ መጠነ ሠፊ ክልላዊ ግጭትነት ሊለወጥ ይችላል የሚል ስጋት እያየለ በመጣበት ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ አጋር ለሆነችው እስራኤል ድጋፋቸውን ለማሳየት ነገ ረቡዕ ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚያመሩ ብሊንከን ገለጡ። ከእርሳቸው አስቀድሞም “ባይደን ከአረብ መሪዎች ጋር ለመገናኘት ወደ ዮርዳኖስ ይሄዳሉ” ሲሉ የዋይት ሀውስ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃን ኪርቢም በተመሳሳይ ተናግረው ነበር።

በተያያዘ፡ በጋዛ ሰርጥ ያለው የሰብአዊ ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ፡ ከለጋሽ ሀገራት የሚገኝ ሰብዓዊ ዕርዳታ በጋዛ ለሲቪሎች የሚደርስበትን ሁኔታ የሚያስችል እቅድ ለማውጣት ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል መስማማታቸውን ተናግረዋል። ዕቅዱ ሲቪሎችን ከጉዳት ማራቅ የሚያስችል አካባቢ ለመፍጠር የሚያግዙ መንገዶችን ማፈላለግም እንደሚጨምር ታውቋል።

በጋዛ ሰርጥ ያለው ሰብአዊ ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል ከለጋሽ ሀገራት ሰብዓዊ ዕርዳታ በጋዛ ሲቪሎች እንዲደርሱ ለማስቻል እቅድ ለማውጣት ተስማምተዋል ሲል ብሊንከን አክለዋል።

ባለፈው መስከረም 26/2016 ዓም የጀመረው የእስራኤል እና የሃማስ ጦርነት በሁለቱ ወገኖች ላይ ካደረሰው ጉዳት አንጻር ከአሁን ቀደም በጋዛ ከተካሄዱት አምስት ጦርነቶች የከፋው መሆኑም ተዘግቧል። እስካሁን 2, 778 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን እና ሌሎች ቁጥራቸው 9, 700 የሚደርሱ መቁሰላቸውን የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሲያስታውቅ፤ በእስራኤል በኩል ቁጥራቸው ከ1, 400 በላይ ዜጎች መገደላቸውን እና ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ 199 ሰዎች በሃማስ ታግተው ወደ ጋዛ መወሰዳቸውን እስራኤል ገልጻለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG