በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድስ ስቴትስ ለሱዳን ልትሰጥ ያሰበቸውን እርዳታ እንደያዘች ትቆያለች


የተቃውሞ ሰልፍ ካርቱም፤ ሱዳን
የተቃውሞ ሰልፍ ካርቱም፤ ሱዳን

በዚህ ሳምንት ሱዳንን የጎበኙት ሁለት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች የሱዳን ወታደራዊ ገዥዎች መፈንቅለ መንግሥቱን የሚቃወሙ ሰላማዊ ሰልፈኞችን መግደል እስኪያቆሙና የሲቪል ሽግግር አስተዳደሩን በቦታ እስኪመልሱ ድረስ ዩናይትድ ስቴትስ ለሱዳን ልትሰጥ ያሰበችውን የእርዳታ ገንዘብ እንደያዘች የምትቆይ መሆኑን ዛሬ ሀሙስ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ሁለቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ስታተርፊልድ የጋራ መግለጫቸውን ያወጡት ለሁለት ቀናት ሱዳን ከጎበኙ በኋላ ነው፡፡

ዲፕሎማቶቹ ከሱዳን ወታደራዊና የሲቪል መሪዎች ጋር ተገናኝተው የመከሩ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የዲፕልማቶቹ ጉብኘት ሱዳን ባለፈው ጥቅምት የተካሄደውን ወታደራዊ የመንፈንቅለ መንግሥት ተከትሎ ከገባችበት ቀውስ የምትወጣበትን መንገድ ለመርዳት መሆኑን በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በሱዳን መፈንቅለ መንግሥቱ ከተካሄደ በኋላ እስካሁን በተነሳው ቀውስ 72 የሚደርሱ ተቃዋሚ ሰልፈኞች መሞታቸው የተገለጸ ሲሆን ባለፈው ሰኞ ብቻ ሰባት ሰዎች መገደላቸው በሮይተርስ ዘገባ ተመልከቷል፡፡

XS
SM
MD
LG