በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል በሶማልያ ጠረፍ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ጋንዳረሽ በተባለው የሶማልያ ጠረፍ አካባቢ ቅዳሜና ዕሁድ በአካሄደው ሥድስት ዙር የአየር ድብደባ 62 የፅንፈኛው አል ሸባባ አማጽያን መግደሉን ገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ኃይል ጋንዳረሽ በተባለው የሶማልያ ጠረፍ አካባቢ ቅዳሜና ዕሁድ በአካሄደው ሥድስት ዙር የአየር ድብደባ 62 የፅንፈኛው አል ሸባባ አማጽያን መግደሉን ገልጿል።

ባለፈው ቅዳሜ በተካሄዱት አራት የአየር ድብደባዎች 34 የአል ሸባባ አማጽያን መገደላቸውን፣ ትላንት ዕሁድ ደግሞ 28 አማጽያን በሁለት ተጨማሪ አየር ድብደባዎች እንዳተገደሉ የአፍሪካው ኮማንድ ወይም ዕዝ ተናግሯል።

“የአፍሪካ ኮማንድና የሶማልያ አጋሮቻች የአየር ድብደባ የአካሄዱት አሸባሪዎች ለወደፊት ጥቃት ለማካሄድ ለማሴር፣ ለመምራት፣ ለማነሳሳትና ለመመልመል በቀላሉ የማይደረስባቸው ቦታዎችን እንዳይጠቀሙ ለመግታት ነው” ሲል የአፍሪካ ዕዝ አስገንዝቧል።

በአየር ድብደባው የተገደሉም ሆነ የቆሰሉ ሲቪሎች የሉም ይላል የአፍሪካ ኮማንድ።

ለብዙ ዓመታት ከአል ሽባብ ጋር ሲዋጋ የቆየውን የሶማልያ መንግሥትን ለመርዳት የአፍሪካ ኮማንድ ሶማልያ ውስጥ የአየር ድብደባ ሲያካሄድ ቆይቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG